ታህሳስ 8 ቀን 2018 ዓ.ም
በጎፋ ኢንዱስሪያል ኮሌጅ የቴክኖሎጂ ልማትና ኢንዱስትሪ ኤክስቴንሽን ዳይሬክቶሬት አዘጋጅነት ከንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ 7 ወረዳዎች የተውጣጡ የኢንተርፕራይዝ ዘርፍ የሚደግፉ ቡድን መሪዎች እና ባለሙያዎች እንዲሁም የኮሌጁ የኢንዱስትሪ ኤክሰቴንሽን እና ኢንኩቤሽን ባለሙያዎችን ያካተተ በካይዘን ፍልስፍና ላይ ስልጠና ተሰጥቷል።
ሥልጠናውን የሰጡት አሰልጣኝ ማህሌት ከበደ የካይዘን ምንነት፣ ጠቀሜታና አተገባበር ላይ ሰፋ ያለ ማብራሪያ የሰጡ ሲሆን የተለያዩ ሀሰቦች ከተሳታፊዎች ለተነሱ ጥያቄዎች ማብራሪያ ተሰጥቶባቸዋል።
ሥልጠናው ያስፈለገበትን ምክንያት የገለጹት የቴክኖሎጂ ልማትና ኢንዱስትሪ ኤክስቴንሽን ም/ዲን ዶክተር ጫላ ፈዬራ በኢንዱስትሪ ኤክስቴንሽንና ኢንኩቤሽን አገልግሎት አሰጣጥ ላይ ሁሉም በሥራው የሚሳተፉ አካላት ተመሳሳይ ግንዛቤና እውቀት ኖሯቸው የካይዘን ፍልስፍናን ተግባራዊ በማድረግ የኢንተርፕራይዞቻችንን ሁሉ አቀፍ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ነው ብሏል።
ጎኢኮ ኮምኒኬሽን !!
.