ታህሳስ 9/2018ዓ.ም
ለኮሌጁ ጎፋ ጋብርኤል ቅርንጫፍ ሰልጣኞች ስለ ኤችአይቪ ኤዲስ ግንዛቤ ማጠናከሪያ ስልጠና ተሰጠ።
በስልጠናው ላይ ተገኝተው የመክፈቻ ንግግር ያደረጉ የኮሌጁ የጎፋ ጋብርኤል ቅርንጫፍ ም/ዲ #አቶ ሃብታሙ ሽታዬ ይህን ስልጠና አዲስ ሆኖ ሳይሆን በመዘንጋት እና ትኩረት ባለማድረግ ተጋላጭ እንዳት ሆኑና በናንተ ለቤተሰቦቻቹ እንዲሁም ለአከባቢ ማህበረሰብ ግንዛቤ እንድትፈጠሩ ጭምር አንዲረዳቹ ነው ብሏል ። እኛ ስለእናንተ እንደምናስበው ሁሉ እናንተም ሃላፊነት በተሞላ መልኩ ኑሮን እንድት መሩ እንፈልጋለን በማለት መልክታቸውን አስተላልፏል ።
ስልጠናውን የሰጡት ተጋባዥ የወረዳው ጤና ባለሙያ ስሆኑ የወጣቶች ስነ-ተዋልዶ ጤና (Adolescent and Youth Reproductive Health) በሚል ርዕስ ላይ ሲሆን የወጣቶች ስነ-ተዋልዶ ጤና ለወደፊት ህይወት ስኬት እና ለጤናማ ማህበረሰብ ግንባታ መሰረት መሆኑን ፣ወጣቶች የወጣትነት የዕድሜ ክልል ውስጥ በሚያልፉበት ጊዜ አካላዊ፣ ስነ-ልቦናዊ እና ማህበራዊ ለውጦች ስለሚገጥሟቸው ትክክለኛ መረጃ ማግኘት በጣም አስፈላጊ መሆኑን በመግለፅ በተለይ ስለ ኤች.አይ.ቪ (HIV) ወጣቶች ሊያውቋቸው የሚገቡ በማለት እንዴት ከኤች.አይ.ቪ መጠበቅ እንዳለበት ፣ለቫይረሱ ተጋላጭ ከሆኑ ነገሮችን እንዴት እራስን መጠበቅ እንዳለበት በሰፊ አንስቶ ማብራሪያ ስቷል ።
ሰልጣኞቹም በተሰጣቸው ስልጠና ግንዛቤ እንዳገኙ በመግለፅ ጥያቄ እና ማብራሪያ የሚፈልጉ ሃሳቦችን አንስተዋል ።
በመጨረሻም የጤና ባለሙያዎች በተጠየቁት ላይ ምላሽ እና ማብራሪያ በመስጠት መረሃ ግብሩ ተጠናቋል ።
ጎኢኮ ኮሚኒኬሽን !!
.