Administration በኮሌጁ አቅራቢያ ለሚገኙ የመንግስትና የግል ከፍተኛ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የግንዛቤ ማስጨበጫ መርሀግብር ተካሄደ ።

በኮሌጁ አቅራቢያ ለሚገኙ የመንግስትና የግል ከፍተኛ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የግንዛቤ ማስጨበጫ መርሀግብር ተካሄደ ።

30th June, 2025

በኮሌጁ አቅራቢያ ለሚገኙ የመንግስትና የግል ከፍተኛ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች አመራሮች በ አዲሱ ቴ/ሙያ ስትራቴጂ የክህሎት ልማት እሳቤዎች ላያ የግንዛቤ ማስጨበጫ እና የኮሌጁን ጎብኘት መርሀግብር  ተካሄደ ።

ሐሙስ -   ሰኔ 19/2017ዓ.ም

በዛሬው እለት በጎፋ ኢንዱስትሪያል ኮሌጅ አቅራቢያ ለሚገኙ 16 የመንግስትና የግል 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት  አመራሮች በኮሌጁ ውስጥ እየተሰሩ ያሉት መሰረተ ልማቶችና ዲፓርትመንቶችን ጉብኝት በማድረግ እና  በአዲሱ ቴ/ሙያ ስትራቴጂ የክህሎት ልማት እሳቤዎች በተዘጋጀው  ሰነድ ላያ ግንዛቤ ተሰቷቸዋል ።

መርሀግብሩ ላይ የተገኙት  ሰዲልለኢትዮጲያ ፣ፊትአውራሪላቅአድገህ፣ ከፍተኛ 23፣ ፋና 02፣ለቡ 2ኛደ/ት/ቤት፣ግንቦት 20 ፣ላፍቶ2ኛደ/ት ቤት፣ እውቀትለህብረት፣ ዋቶ2ኛደረጃት/ቤት፣ፈለገነዋይአካዳሚ፣ ነዋይቻሌንጅ አካዳሚ፣ሳውዝዌስትአካዳሚ

፣ሪደምሸንአካዳሚ፣ ፊውቸር ሆፕ ጀነሬሽን፣ ኪድስኒውፍላወር እና  ብስራተ ገብርኤል አካዳሚ ናቸው ።

የተዘጋጀው ሰነድ አዲሱ ቴ/ሙያ እሳቤዎችን በሰፊው የዳሰሰ ስሆን ሰነድ የቀረቡት የኮሌጁ የ research and publication አስተባባሪ #አቶ ቱራ ነጋሳ ናቸው ።

በሰነዱ የመወያያ መነሻ ሃሳብ በኮሌጁ ዋና ዲን #ዶክተር አሸብር ተክሌ እና ስልጠና እና አካዳሚክ ጉዳዮች ም/ዲን አቶ ጋዲሳ አበበ መድረክ መሪነት ውይይት ተደርጓል ።

የ ውይይቱ ዋና አላማ ከቀረበው ሰነድ በተጨማሪ ኮሌጁ እና ት/ቤቶች እንዴት በተሻለ መልክ ተቀራርቦ መስራት እንዳለባቸው ፣በ2018 ዓ.ም አድስ ተማሪ ቅበላ በተመለከተ ፣ከት/ቤት የፈጠራ ችሎታ ያላቸው ተማሪዎቹ  እንደት ወደ ኮሌጁ በመምጣት የፈጠር ችሎታቸውን ማዳበር የሚችሉበት አላማውን ያደረገ ነበረ ።

ከተሳታፊዎች በተነሳው ሃሳቦች በመርሀግብሩ ላይ የተገኙት በኮሌጁ አመራሮች  ምላሽ እና ማብራሪያ በመሰጠት ተማርዎቻቹ   አዲሱ የ/ቴ/ሙ/ስትራቴጂ የክህሎት ልማት እሳቤዎች ግንዛቤ ከተፈጠረላቸው ምርጫቸውን TVT    እንደሚያደርጉ አንጠራጠርም  ለዚህ ደግሞ አንድ ላይ በመሆን  አሁን በኮሌጁ እየሰለጠኑ ካሉት ሰልጣኞች በተሻለ   በ2018 በጀት አመት በቁጥር የተሻለ ሰልጣኝ ተቀብለን ለማሰልጠን እንሰራበታለን በማለት መልክታቸውን በማስተላለፍ ተጠናቋል ።

ጎኢኮ ኮሚኒኬሽን !!

.

Copyright © All rights reserved.

Created with