Administration የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የስነ-ልቦና ትምህርት ቤት እና ጎፋ ኢንዱስትሪ ኮሌጅ ጨምሮ 4 ኮሌጆች የጋራ መግባቢያ ስምምነት ተፈራረሙ

የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የስነ-ልቦና ትምህርት ቤት እና ጎፋ ኢንዱስትሪ ኮሌጅ ጨምሮ 4 ኮሌጆች የጋራ መግባቢያ ስምምነት ተፈራረሙ

23rd July, 2026

የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የስነ-ልቦና ትምህርት ቤት እና ጎፋ ኢንዱስትሪ ኮሌጅ ጨምሮ 4 ኮሌጆች የጋራ መግባቢያ ስምምነት ተፈራረሙ

      ሰኔ 11/2018ዓ.ም

የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የስነ-ልቦና ትምህርት ቤት (AAU) እና ጎፋ ኢንዱስትሪ ኮሌጅ ፣አቃቂ ፖል ቴክኒክ ኮሌጅ፣ አአ ተግባረዕድ ፖል ቴክኒክ ኮሌጅ እና ልደታ ማኑፋክቸሪንግ ኮሌጅ በጋራ ለመስራት የሚያስችላቸውን ታሪካዊ የመግባቢያ ስምምነት (MoU) በዛሬው እለት ተፈራርመዋል።

​ይህ በተቋማቱ መካከል የተደረገው ስምምነት በ አአ ከተማ አስተዳደር ሥራና ክህሎት እና በጀርመን ዓለም አቀፍ ትብብር ድርጅት (GIZ) ስር  የጥራት ማሻሻያ ፕሮግራም (GIZ-QEP II) ትብብር መሆኑ ተገልጿል።

​የዚህ ስምምነት ዋና ዓላማ በከፍተኛ ትምህርት እና በቴክኒክና ሙያ (TVET) ዘርፍ መካከል ያለውን ትስስር ማጠናከርና በተለይም  የስነ-ልቦና ዝግጁነት፣ በተማሪዎችና ሰልጣኞች ሁለንተናዊ ብቃት ግንባታ እንዲሁም በአቅም ማሳደግ ዙሪያ በትብብር ለመስራት ያለመ ነው ተባለ ።

በተጋባዥነት  የኮሌጆቹን የስነልቦና አገልግሎት  ተሞክሮ ሰነድ ያቀረቡት የጎፋ ኢንዱስትሪያል ኮሌጅ  የማማከር  አገልግሎት አስተባባሪ አሰልጣኝ ወይንሸት መኮንን በአዲሱ ስትራቴጂ መሰረት አራቱ ኮሌጆች ሰልጣኞችን ከምዝገባ ጀምሮ እስከ ሥራ ትስስር የሚያግዝ የቪጂሲ (VGC) ማማከር አገልግሎት እየሰጡ መሆናቸውን ገልፀው  በሳይኮሎጂ ባለሙያዎች እጥረት ምክንያት እንደ ራስን መሳትና ተስፋ መቁረጥ ያሉ ተግዳሮቶች ቢያጋጥሙም፤ በተለይም  እንደ ጎፋ ኢንዱስትሪያል ኮሌጅ በGIZ እና በለቤዛ ማዕከል ድጋፍ የጋራ ስልጠናዎችን በመውሰድ የባለሙያዎችን አቅም የማሳደግ ስራ ተሰርቷል ብሎአል ። በአሁኑ ወቅት በአቻ ለአቻ መርሃ-ግብሮች፣ በቡድንና በግል የምክር አገልግሎት እንዲሁም በሪፈራል ሥርዓት ተጋላጭ ወጣቶችንና ሴቶችን በመደገፍ ላይ ሲሆኑ፣ ጉዳዩ በጣም ትኩረት የምፈልገው በመሆኑ ለቀጣይ ስኬታማነትም  ከሚመለከታቸው አካላት  ድጋፍ እንደሚያስፈልግ አብራርተዋል ።

ይህ የፊርማ ስነ-ስርዓት  የተከናወነው በልደታ ማኑፋክቸሪንግ ኮልጅ ስሆን በኮሌጁ VGC ቢሮ ጉብኝት በማድረግ መርሀ ግብሩ ተጠናቋል ።
         ጎኢኮ ኮሚኒኬሽን !!

.

Copyright © All rights reserved.

Created with