ጥር 4 / 2018 ዓ.ም
የቴክኒክና
ሙያ ስልጠና ተቋማት ሴት አመራሮች እና አሰልጣኞችን ተሳትፎ በማሳደግ የሴቶችን ውሳኔ ሰጭነት ሚና ከፍ ማድረግ አላማ ያደረገው ፎረም ሁሉም የኮሌጁ
ሴት አሰልጣኞች እና ሴት አመራሮች በተገኙበት ሰባት 7 የፎረሙ የስራ አስፈፃሚ አባላት ተመርጠዋል ።
የጎፋ
ኢንዱስትሪያል ኮሌጅ ዋና ዲን ዶ/ር አሸብር ተክሌ እንደገለፁት ሀገራችን ከደረሰችበት የእድገት
ደረጃና መካከለኛ ገቢ
ካላቸው ሀገራት ለመቀላቀል በምታደርገው ጥረት
በቴ/ሙያ/ሥልጠና ተቋማት የሴቶችን ሁለንተናዊ ተሳትፎና ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ የወጡ ፖሊሲና ስትራቴጂዎች ለማስፈፀም ፣
የሀገራችን ሴቶች ግሎባላይዜሽን
ከፈጠረው እድል ተጠቃሚና ተወደዳሪ እንዲሆኑ ለማድረግ፣ የሴቶችን ወቅታዊ ፍላጎቶችና ጥያቄዎችን ለመመለስ ፎረም ማቋቋሙ ጥሩ ተግባር ነው ብለዋል ።
ከፌደራል
ስራና ክህሎት ሚኒስተር የተላከውን የሴት አሰልጣኞች እና አመራሮች ፎረም መመስረቻ ማስፈፀሚያ ሰነዱን ያቀረቡት የኮሌጁ የተቋም ልማትና አስተዳደር ጉዳዮች ም/ዲን # ወ/ሮ
ዚነት ሰይድ በበኩላቸው የቴክኒክና
ሙያ ስልጠና ተቋማት ያሉ ሴት አሰልጣኞች እና አመራሮች በጋራ ጉዳያቸው ዙሪያ የሚመክሩበት፤ ልምድ ልውውጥ የሚያካሂደበትና ለተሻለ ለውጥ አቅጣጫ የሚያስቀምጡበት ስብስብ እንደሆነ ገልጾ በቴክኒክና ሙያ
ስልጠና ተቋማት ለሴት ሰልጣኞች፣አሰልጣኞች እና አመራሮች ምቹ የስልጠና ሁኔታ ለመፍጠር፣ የሴት አሰልጣኞችንና አመራሮችን ተሳትፎና ተጠቃሚነት ለማሳደግ የመተጋገዝ የመደጋገፍና ልምድ የመጋራት ባህላችንን በተደራጀ መንገድ ተግባራዊ በማድረግ ብቁ፣ ተወዳዳሪና ወቅቱ የሚጠይቀውን ክህሎት በመለበስ ኢኮኖሚያዊ ማህበራዊና ፖለቲካዊ ተጠቃሚነታችን በማሳደግ ለሀገር ዕድገት የድርሻችንን መወጣት ይገባል ሲሉ ገልጸዋል ።
ጎኢኮ ኮምኒኬሽን !
.