Administration የጎፋ ኢንዱስትሪያል ኮሌጅ የዛሬው የወርቃማው ሰኞ የአብሮነት እና የእውቀት ሽግግር የሥራና የሕይወት ሚዛን ጥበቃ (Work-Life Balance) ላይ ያተኮረ የክህሎት ማሳደጊያ ለይ ተካሄደ

የጎፋ ኢንዱስትሪያል ኮሌጅ የዛሬው የወርቃማው ሰኞ የአብሮነት እና የእውቀት ሽግግር የሥራና የሕይወት ሚዛን ጥበቃ (Work-Life Balance) ላይ ያተኮረ የክህሎት ማሳደጊያ ለይ ተካሄደ

21st July, 2026

የጎፋ ኢንዱስትሪያል ኮሌጅ የዛሬው የወርቃማው ሰኞ የአብሮነት እና የእውቀት ሽግግር የሥራና የሕይወት ሚዛን ጥበቃ (Work-Life Balance) ላይ ያተኮረ የክህሎት ማሳደጊያ ለይ ተካሄደ

ሃምሌ 13/2018ዓ.ም

በሥራ ቦታዎች ላይ የሚፈጠሩ የአእምሮ ውጥረቶችን ለመቀነስና የሠራተኞችን ሁለንተናዊ ደህንነት በመጠበቅ ተቋማዊ ምርታማነትን ለማሳደግ ያለመ የሥራና የሕይወት ሚዛን ጥበቃ (Work-Life Balance) የዕውቀት ሽግግር ከ አአ ዩኒቨርስቲ የመጡ የሳይኮሎጂ ባለሙያዎች ተሰጥቷል።

የእውቀት ሽግግሩ ሠራተኞች በሙያዊ የሥራ ኃላፊነታቸውና በግል ሕይወታቸው መካከል ጤናማ ሚዛን መፍጠር የሚችሉባቸውን ስልቶችና ተግባራዊ ክህሎቶች ለማስጨበጥ ታስቦ የተዘጋጀ ነው።

በአሁኑ ወቅት በሥራ ቦታዎች ላይ የሚገጥሙ ተደራራቢ ኃላፊነቶችና የአእምሮ ውጥረቶች በሠራተኞች ጤና፣ ማኅበራዊ ሕይወትና በሥራ አፈጻጸም ላይ ከፍተኛ ተፅዕኖ እያሳደሩ ይገኛሉ። ይህንን ተግዳሮት ለመቅረፍም ጊዜን በአግባቡ የመጠቀም፣ ቅድሚያ የሚሰጣቸውን ጉዳዮች የመለየትና በሥራና በቤተሰብ ሕይወት መካከል ግልጽ ድንበር ማበጀት እንደሚገባ በሰፊው ተብራርቷል።
ሰራተኞች የሥራ ሰዓታቸውን በብቃት በመጠቀም አስቸኳይና አስፈላጊ የሆኑ ተግባራትን ለይተው የሚያከናውኑበት ሥልት፣በሥራ ጫና ምክንያት የሚመጣን ውጥረት ለመቀነስ የሚያግዙ የአእምሮና የአካል እረፍት ልምምዶች፣በሥራ ቦታም ሆነ በቤት ውስጥ ጤናማ የሥራ ድባብ ለመፍጠር የሚያስችሉ የሐሳብ ልውውጦችና ፣ በቂ እረፍትና አካላዊ እንቅስቃሴ ለሥራ ስኬትና ለግል ደስታ ያላቸውን ሚና ማሳየት ዋና የዛሬ የዕውቀት ሽግግር እንደነበረ ተገልጿል።

                   ጎኢኮ ኮሚኒኬሽን !!

.

Copyright © All rights reserved.

Created with