Administration እንኳን ደስ አለን እንኳን ደስ አላችሁ

እንኳን ደስ አለን እንኳን ደስ አላችሁ

23rd July, 2026

👏እንኳን ደስ አለን ✨👏እንኳን ደስ አላችሁ
የጎፋ ኢንዱስትሪያል ኮሌጅ ዓለምአቀፉን የISO 21001:2025 የጥራት ደረጃን በማሟላት በዛሬው ቀን 01/11/2018 ዓ.ም ለዕውቅና ሰርተፊኬት ታጨ::
የጎፋ ኢንዱስትሪያል ኮሌጅ ሁለቱንም ካምፓሶቹን ያካተተ የዓለምአቀፍ ደረጃውን የጠበቀ የትምህርት ተቋም አመራር ስርዓትን በተሳካ ሁኔታ በመተግበሩ የISO 21001:2025 ዕውቅና እጩ መሆኑ ተረጋግጧል።
ኮሌጁ ላለፉት ወራት የትምህርትና ስልጠና ጥራትን ለማረጋገጥ እንዲሁም የአሰራር ስርዓቱን ዘመናዊና ዓለምአቀፋዊ ለማድረግ ሰፊ የዝግጅት ስራዎችን ሲያከናውን ቆይቷል። ተቋሙ ተግባራዊ ያደረገውን ይህንን የትምህርት ተቋም አመራር ስርዓት (EOMS) ተከትሎ ከኢትዮጵያ ተስማሚነት ምዘና ኤጀንሲ (ECA) በመጡ ከፍተኛ ባለሙያዎች የውጭ ኦዲት (External Audit) ተደርጎ ኮሌጁ ደረጃው የሚጠይቃቸውን መስፈርቶችና የአሰራር ጥራቶች ሙሉ በሙሉ አሟልቶ በመገኘቱ ብቁ መሆኑ ተረጋግጦ ለዕውቅና እጩ ለመሆን መብቃቱ ታውቋል።
በመሆኑም ይህ ታሪካዊ ስኬት የተቋሙ አመራር፣ አሰልጣኞች፣ ደጋፊ ሰራተኞች እና ሰልጣኞች በጋራና በቁርጠኝነት ያደረጉት ከፍተኛ ጥረት ውጤት በመሆኑ እንኳን ደስ አለን እንኳን ደስ አላችሁ እያልን ይህ እጩነት ተቋሙ የጀመረውን የጥራት ጉዞ አጠናክሮ በመቀጠል፣ የቀጣይ ትውልድ ምሳሌ የሚሆን የቴ/ሙያ ማሰልጠኛ ኮሌጅ ለመሆን የሚያስችለውን ትልቅ መነቃቃት የሚፈጥር መሆኑን አመልክቷል።

ጎፋ ኢ/ኮ ኮሚኒኬሽን!!

.

Copyright © All rights reserved.

Created with